መስከረም 4 ቀን ሊካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው በሚል መስከረም 4፣ 2012 ዓ.ም  ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ጥቅምት 30 ተራዘመ።

የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ ሲባል ሰልፉ ወደ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም መዘዋወሩን  አስታውቀዋል።

አስተባባሪዎቹ  ከድሬዳዋና ሐረሪ ክልሎች ውጪ የፌደራል መንግስትን ጨምሮ ከቀሪዎቹ ክልሎች ጋር መወያየታቸውን አስታውሰው፤  የተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ሃላፊዎች ሰልፉ እንዲራዘም በመጠየቃቸው ሰልፉን ሊራዘም መቻሉን ተናግረዋል።

አስተባባሪዎቹ አክለውም በየጊዜው ከመንግስት ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን በየ15 ቀኑ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።