ግምቱ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ

ግምቱ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ።
በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉምሩክ በኩል ሊያልፍ ሲል ግምቱ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ መያዙን የገቢዎች ሚኒስትር አስታወቀ።

በቦልቪያናዊዉ ናማኒ ቺንቼ ኢቬሊን የፓስፖርት ቁጥር AE57255 ከብራዚል ሳዖ ፖሎ አዲስ አበባ የገባዉ 8 ኪሎ ግራም የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የጉምሩክ ፈታሾች በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉ ተነግሯል።

አደንዛዥ እጹ የተያዘው ከብራዚል ሳኦ ፖሎ ጀምሮ በጉምሩክ ኮሚሽን ኢንተለጀንስ ቡድን ባደረገዉ የተቀናጀና ጠንካራ ክትትል መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ባለፈዉ ሳምንትም 20 ሚሊየን ብር የሚገመት 10.8ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ መያዙ የሚታወስ ነዉ፡፡