የዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ስራ ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

የዩኒቨርሲቲዎች የ2012 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ ሰላማዊ እና ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ከተማሪዎች አገልግሎት ሃላፊዎች፣ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር በ2012 የትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ላይ የቀጥታ ቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ውይይት አካሂደዋል፡፡

የተማሪዎች ቅበላና የቅበላ ዝግጅቶችን፣ የቅበላ አይነቶችን፣ የተማሪዎች ምደባና ዝውውርን፣ ስልጠናዊ ውይይትን፣ የአዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች አካሄድን፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ዳሰሳ፣ የተለያዩ በ2012 ተግባራዊ የሚደረጉ ህጎች እና እንዲሁም የአሰራር ድጋፍና ክትትሎችን አጀንዳ ዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይታቸው ላይም ዩኒቨርስቲዎች የ2012 የትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍን በማጠናቀቅ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው ተገልጾላቸዋል፡፡

የመማር መስተማር ስራውን ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ተቋማት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡ (ምንጭ:- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)