ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአባ ገዳዎችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በእሬቻ በዓል አከባበር ዙሪያ ከአባ ገዳዎችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የእሬቻ በዓል የኦሮሞ ባህል እሴትና መርህ በሆኑት የአንድነት፣ የፍቅርና የይቅርታ መሠረቶች ላይ በመመርኮዝ በሰላማዊ መንገድ መከበር እንዳለበት ተወስቷል።

አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ክብረ በዓሉ በሰላማዊ መንገድና ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት የሚያከብሩት የደስታ በዓል እንዲሆን ባለድርሻ አካላት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ባለፈም ከመላ ኢትዮጵያውያን ጋር በመናበብ እሴትን፣ ቋንቋንና የኦሮሞ ህዝብ ባህልን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሰራ ተመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእሬቻ በዓል ዝግጅትና አከባበር ሰላማዊና አንድነታችንን ባንጸባረቀ መልኩ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ የክልሉን ነዋሪዎች የሚመለከቱ የልማት፣ የሰላምና ለውጡን የማስቀጠል ስራዎች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም ከአባ ገዳዎችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከጠቅለይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።