በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ እያካሄዱ ነው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና ካሕናት በባሕር ዳር፣ ቢቸና፣ ቡሬ፣ እንጅባራ፣ መርዓዊ፣ ወልድያ፣ ፍኖተ ሠላም፣ ደባርቅ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ቆቦ፣ ማጀቴ፣ ጫጫ፣ ዋድላ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ዳባት፣ መሐል ሜዳ፣ ውጫሌ፣ ሮቢትና፣ ላልይበላ ሰልፎች እያካሄዱ ነው፡፡  

በተጠቀሱት ከተሞች በምዕመናን እና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በሰልፉ ላይ “በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም! በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ!” የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡