የትምህርት ተቋማት የአካዳሚ ቴክኒክ ረዳቶችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚቀርፍ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የአካዳሚ ቴክኒክ ረዳቶችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መቅረፍ የሚያስችል ደንብና መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።

በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብና መመሪያ ዙሪያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረክም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ደንብና መመሪያው የሰራተኞችን መብትና ግዴታ እንዲሁም የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ለማስከበር የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

ይህም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ነው የተባለው።

ረቂቅ ደንብና መመሪያው በቀጣይነት በሚደረጉ ተጨማሪ ውይይቶች ከዳበረ በኋላ የሚጸድቅ መሆኑም ተመላክቷል።