ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በቱሪዝም ዘርፍ ላደረጉት አስተዋፅኦ የአለም ቱሪዝም ድርጅት የ2019 ተሸላሚ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቱሪዝም ዘርፍ ላደረጉት አስተዋጽኦ የ2019 የአለም ቱሪዝም ድርጅት የ2019 ተሸላሚ ሆኑ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱን ከወርልድ ቱሪዝም ፎረም ፕሬዚዳንት ቡሉት ባጊቺ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ላስመዘገበችው እመርታ ማሳያ እንዲሆንም የ2012 የአለም የቱሪዝም ጉባኤን እንድታስተናግድ የተደረሰው ስምምነት ሰነድም ቀርቧል::

የልኡካን ቡድኑ የብሄራዊ ሙዚየም እድሳት ሥራን የጎበኙ ሲሆን ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል::