ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የሙዚቃው ሰው ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ኤልያስ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ ጊታርና ፒያኖ ተጫዋች ሲሆን፥ አዳዲስ ሙዚቀኞችን ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አስተዋውቋል።  

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተ ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል።

በተጨማሪም ከመሃሙድ አህመድ፣ ከፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ከአለማየሁ እሸቴ፣ ቴዲ አፍሮ፣ እዮብ መኮንን፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ልኡል ሀይሉ፣ ሀይሌ ሩትስ፣ ሚካያ በሃይሉ፣ ትግስት በቀለ፣ ቤሪ እና ዳን አድማሱ ጋር አብሮ በመስራት በሙያው አሻራውን አኑሯል፡፡

ከዜማ ላስታስና ከአፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋርም የሰራበት ጊዜ ነበር። ኤልያስ ከ40 በላይ ሙሉ አልበሞችን አቀናብሯል። ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስኳር እና ኩላሊት ህመም ገጥሞት ህክምናውን የቆየ ቢሆንም ሕመሙ ተባብሶበት በሆስፒታል ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል፡፡