ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የዓለም የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን በማስመልከት የሰላም ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡

በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚሊኒየም አዳራሽ የሚከናወነው ይህ የደስታ መግለጫ ዝግጅት እሁድ ጥቅምት 9፣2012 ዓ.ም ከቀኑ 11 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንደሚዘልቅ የሰላም ሚኒስቴር ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የ2012 ኖቤል ሰላም ሎሬት ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል፡፡