በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊስ ዙሪያ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊስ ዙሪያ ያተኮረ  መድረክ በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ነው፡፡

በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ከ250 በላይ የውጪ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ባለሙያዎች ፣ የልዩ ልዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም የኢጋድ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡

በሰላም  ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ኢትዮጵያ በፈጣን ሀገራዊ ለውጥ ላይ እንደምትገኝ ገልፀው ፤ ለዘላቂ ሰላምና ቀጣናዊ ትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታው አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ በበኩላቸው መሰል መድረኮች ጠቃሚ ሀሳብ የሚንፀባረቅባቸው በመሆኑ ለፖሊሲ ማሻሻያ ግብዓት ሆነው ያገለግላሉ ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ በለውጥ ተስፋ መንገድ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሚኒስትር ድኤታው፤  ቀጣናዊ ትስስርን በማሳደግ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ እንዲጠናከር የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የዓለም የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላደረገችው ጥረት እውቅና የሰጠእንደሆነ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

መድረኩ ለሁለት ቀናት ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡