ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከ4 አስርት አመታት በኋላ የንግድ በረራ መጀመራቸዉ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ አውሮፕላንም ቅዳሜ ዕለት የመጀመሪያውን በረራ ወደ ሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሾ ማድረጉ ተሰምቷል።
የበረራዉ መጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከቀጠናዉ ሀገራት ጋር የጀመሩትን የሰላም ሂደት ከማጠናከሩም ባለፈ ምስራቅ አፍሪካን በምጣኔ ሃብት ለማዋሃድ የሚደረገውን ጥረትም ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ተብሎለታል።