ደቡብ ሱዳን በሌሎች ሃገራት የሚገኙ 39 ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው

ደቡብ ሱዳን በሌሎች ሃገራት የሚገኙ 39 ኢምባሲዎቿን በፋይናስ እጥረት ምክንያት ልትዘጋ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማዊን ማኮል አገሪቱ በውጭ አገር የሚገኙ ኤምባሲዎችዋን ለማስተዳደር አስቸጋሪ ሆኖባታል ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ኤምባሲዎቹ በቅርብ ግዜ እንደሚዘጉም አስታውቀዋል፡፡

አገሪቱ ከዚህ ቀደም ስራቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያለቻቸውን 40 ዲፕሎማቶች ከስራ ማሰናበቷ የሚታወስ ነው፡፡

በነዳጅ ምርት ላይ ኢኮኖሚዋ የተንጠነጠለው ደቡብ ሱዳን በ2013 በጀመረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ምርትዋን መቀነሱ እና የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ይገለፃል፡፡

በአገሪቱ ሙስና መስፋፋቱ እና የፖለቲካ አለመረጋጋት የፋናንስ ቀውስ ማስከተሉም ተገልጿል፡፡

(ምንጭ፡-ዘ ኢስት አፍሪካ)