አፍሪካ የሩዝ ምርቷን በእጥፍ ለማሳደግ እንድትችል ጃፓን ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

በጃፓን ዮኮሃማ ከተማ የአፍሪካ መሪዎች በተሳተፉበት ኮንፈረንስ ላይ አፍሪካ እ.ኤ.አ. በ2030 የሩዝ ምርቷን በእጥፍ ማሳደግ እንድትችል ጃፓን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች፡፡

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በአፍሪካ ልማት ላይ በሚመክረው የቶኪዮ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር የጃፓን ቴክኖሎጂና ፈጠራ ይህን ግብ ለማሳካት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

ዕቅዱ አፍሪካ በ11 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 50 ሚሊዮን ቶን ስንዴ እንድታመርት መርዳት ነው፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክም እቅዱ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የተገለጸው፡፡

"የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና በበኩላቸው፣ ምንም እንኳን በግብርናው መስክ የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም፣ ዓለም አቀፉን የፀረ-ርሃብ ትግል በአሸናፊነት እየተወጣ አይደለም። ሁላችንም በአንድነት መነሳት እና በዓለም አቀፍ ርሃብን ደረጃ ማጥፋት አለብን ፡፡ ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ በአፍሪካም ርሀብን ማጥፋት አለብን" ብለዋል፡፡

ጃፓን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የእርሻ ምርታማነትን ለማሻሻል እንደ አንድ አካል በመሆን አነስተኛ የአፍሪካ ገበሬዎች አምርተው ከመመገብ ባለፈ ምርት እስከ መሸጥ ደረጃ እንዲደርሱ ለመቀየር ተስፋ ታደርጋለች ነው የተባለው፡፡

ናይጄሪያ እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ የሩዝ ምርቷን ለማሳደግ ጥረት እያደረገች እንደሆነ በጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-ቢቢሲ)