በጋምቢያ በጃሜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታሰሩ በሙሉ መለቀቃቸው ተመለከተ

የጋምቢያ ፕሬዝደንት አዳማ ባሮዉ አማካሪን ማይ ፋቲ በጃሜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታሰሩ በሙሉ መለቀቃቸውን አስታወቁ  ።

የጠቀሰዉ የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘገባ እነዚያ የታሠሩት በሙሉ እንዲለቀቁ የተገደረጉት ከጸጥታ ጉዳይ ኃላፊዎች ጋር በተካሄደው ዉይይት ነው ብለዋል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዳሜ ዕለት ያህያ ጃሜህ ጋምቢያን ለቀዉ ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከሄዱ በኋላም ተጨማሪ የምዕራብ አፍሪቃ ወታደራዊ ኃይል እሁድ ዕለት ወደ ጋምቢያ መግባቱን ነው የተገለጸው ።

የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማህበረሰብ ኤኮዋስ ባለስልጣናት የስልጣን ክፍተት እንዳይፈጠር አዲሱ ፕሬዝደንት ባሮዉ በፍጥነት ወደ ባንጁል መግባት እንዳለባቸዉ አመልክተዋል።

የባሮዉ አስተዳደር ስልጣኑን በይፋ ሲረከብም ሀገሪቱ በፋይናንስ በኩል እጥረት ሊገጥማት እንደሚችልም ጠቁመዋል-(ዶችይዌለ) ።