አሚሶም በአልሻብ የተያዙ ይዞታዎችን በማስመለሱ የአፍሪካ ህብረት አድናቆቱን ገለጸ

የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ኮሚሽን  አሚሶም   በአልሸባብ  ተይዘው  የነበሩ የተለያዩ  ይዞታዎችን በማስለቀቁ ረገድ  ለተጫወተው ሚና  አድናቆቱን   ገልጿል ።       

አሚሶም  በአፍሪካ  ሽብርተኝነትን ከሚዋጉ  ክፍለ አህጉር ድርጅቶች  በአንጻራዊነት  የተሻለ  እንቅስቃሴ  እያካሄደ  መሆኑን ተናግረዋል ።

የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ኮሚሽነር  ስሜል ቸሩጊ እንደሚናገሩት  ግጭት በሚበዛባት አፍሪካ  በብቃት  የሠለጠኑ ወታደሮችን  ከዓለም  አቀፍ  አጋሮች ጋር በመቀናጀት በማሠማራት   የአክራሪ የተጣቂ ቡድኖች የሆኑትን አልሻባብና ቦኮሃራምን  ለመዋጋት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል ።           

እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ “ በሶማሊያ  የተሠማሩ ወታደሮችን ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በማሠልጠንየተለያዩ ወታደራዊ ጥቃቶች በመክፈት በአልሸባብ የተያዙ  ይዞታዎች  እንዲለቀቁ በማድረግ  በኩል የአሚሶም ወታደሮች  የተሠጣቸውን ተዕልኮ በአግባቡ  እየተወጡ  ይገኛሉ” ብለዋል ።

በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ፕሬዚደንት ሳልቫኪር  ከተለያዩ  ተጻራሪ ቡድኖች ጋር ለመደራደር ተስፋን  የሠጡ መሆናቸውን   የሚገልጹት ኮሚሽነሩ   በምዕራብ  አፍሪካ ቦኮ ሃራምን  ከይዞታዎቹ  እንዲለቅ  ለማድረግ ተከታታይ ዘመቻውን  ተከፍተዋል እንዲዳከምም ሆኗል ።

ሆኖም አሁን ያለቺውና   መንግሥት አልባና የተበታታነች  ሊቢያ  በአገሪቱ   ሰላም  ለማምጣት በተቀናቃኝ ወገኖች መካከል  የሚደረገውን  ድርድር ይበልጥ  አስቸጋሪ እንዳደረገው  ኮሚሽነሩ አስረድተዋል ።  

የአፍሪካ  ህብረት   አባል አገራት   የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን   በመሥጠት   ለአህጉሪቱ   ስጋት  የሆኑትንና  ለግጭት መንስኤ የሆኑ ችግሮችን  አስቀድሞ  ለመከላከል   እየተሠራ እንደሚገኝ  ኮሚሽነር ሰሜል ቸጉሪ አስረድተዋል ።

ባለፈው  ሳምንት   የአፍሪካ ህብረት  ኮሚሽነር በመሆን የተመረጡት  ሙሳ ፋቂ ማህመት እንደተናገሩት  የአህጉሪቱን  ሰላምና ፀጥታ  ማስከበር  ቅድሚያ  የሚሠጠውና   የ 2063   የልማት አጀንዳን  ለማሳካት  ትልቅ እገዛ  የሚኖረው  በመሆኑ  ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ መሆኑን  አስመረው መናገራቸው ይታወሳል ።     

( ትርጉም : በሰለሞን ተስፋዬ)