የአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ ቃለ መሃላ ፈጸሙ

የአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ ቃለ ዛሬ በመቃዲሾ ከተማ ከኤርተራ መሪ በስተቀር የአፍሪካ ቀንድ መሪዎች በተገኙበት ፈጽመዋል፡፡

በሞቃዲሾ እየተካሄደ ባለው በዓለ ሲመት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ፣ እንዲሁም የአፍሪካና የአውሮፓ ሕብረት፣ የአረብ ሊግና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል።

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሰሞኑን ሽብርተኛ ቡድኑን አልሸባብ ባፈነዳው ቦንብ 34 ዜጎችን መግደሉን አንስተው አሸባሪውን ለመዋጋትና ሌች አከባዎችም በአካል በመጎብት በአጠቃላይ የሀገራቸው ሰላም በማረጋገጥ የዜጎች  ኑሮ ለማሻሻል ቃል ገብተዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ምኞት የተረጋጋች ሶማሊያ እንድትፈጠር በመሆኑን ገልጸው ፤አገሪቱ ለቀጠናው መረጋጋት እና ብልጽግና ልትተጋ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

አያይዘውም ሶማሊያ የግጭት ምሳሌ የመሆኗ ታሪክ ለመቀየር የኢትዮጵያ ህዝብ ከሶማሊያ ጎን በመቆም የሚያደርገውን ጥረት አጠመናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀል ፡፡

የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር በበኩላቸው በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ጂቡቲ የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የኬንያው ፕሬዚዳንት ሁሩ ኬኒያታም ሶማሊያ ከ30 አመት ወዲህ የመጀመሪያውን ብሄራዊ ምርጫ ማካሄዷ ብሎም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ማድረጓን የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡