የአልሸባብ ድርጊት የሶማሊያ ህዝብን ፍላጎት የሚፃረር ነው – ፕሬዚደንት አብዱላሂ

አዲሱ የሶማሊያ ተመራጭ ፕሬዚደንት የሆኑት ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብዱላሂ ወይም በቅጽል ስማቸው ፋርማጆ እንደተናገሩት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛው አልሻባብ የሚያከናውናቸው ድርጊቶች  በሙሉ 12 ሚሊዮን ከሚሆነው  የሶማሊያ ህዝብ ፍላጎት ጋር የሚፃረር ነው ብለዋል ።

ፕሬዚደት አብዱላሂ  በተለይ  መንግሥታቸው አክራሪነትን  ለመዋጋት  ቁርጠኛ  መሆኑን  ባመለከቱበት ንግግራቸው እንደገለጹት ወጣቶች እንደ አልሻባብ ያሉ  አክራሪ ቡድኖችን ከመቀላቀል መቆጠብ እንዳለባቸውና በአልሻባብ ቡድን  ውስጥ  የሚገኙ ወጣቶች ቡድኑን  በመክዳት  በአገር ግንባታው ሂደት ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።  

የአሚሶም የፕሬስ መግለጫ እንዳመለከተው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ጠንከራ ሠራዊትን በሶማሊያ ምድር በመገንባት የተፈለገውን ግብዓት በሟሟላት   በአገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እሠራለው ብለዋል ።    

እንደ ፕሬዚደንቱ ገለጻ “ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር  የአክራሪ ቡድኖችን እንዳይቀላቀሉ ጥረት በማድረግ  የሠራዊቱን  ጥቅማጥቅም  በማስከበርና ትጥቁን የተሟላ በማድረግ  የፀጥታ ሃይሉን ይበልጥ  የመገንባት እንቅስቃሴዎች ይካሄዳሉ ”

በተጨማሪም ፕሬዚደንቱ “ ወጣቶች  ከአክራሪ ቡድኖች በመውጣት  ከኛ ጋር ለመሥራት የሚፈልጉ ከሆነ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በአገር ግንባታ አንዲሳተፉ ይደረጋል  እንዲሁም ከአልሻባብና አይኤስ አይኤስ ጋር መሥራታቸውን የሚቀጥሉ ወጣቶች ካሉ ደግሞ  ጊዜው አብቅቷል ” ብለዋል ።

ፕሬዚደንት  የአፍሪካ ህብረት  ሃይል  ከሆነው  አምሶም ጋር የሶማሊያን  በጋራ ለመሥራት  ቁርጠኛ መሆናቸውንና  የጦር ሃይሉ  በሶማሊያ  ሰላምና ፀጥታ  እንዲሰፍን ለዓመታት  ላደረገው ጥረት ክቡር  ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

በአሚሶም  ተልዕኮ  ተሠጥቷቸው  ግዳጃቸውን  እየተወጡ የሚገኙ  ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ውድ ህይወታቸውን ጭምር  በመሰዋት   ለሶማሊያ  መንሰራራት ታላቅ ዋጋ  እየከፈሉ  እንደሆነ ማስተዋላቸውን  በንግግራቸው አመልክተዋል ።