በደቡብ አፍሪካ በተካሄደ ሰለፍ ፖሊስና ሰልፈኞች ተጋጩ

በደቡብ አፍሪካ  ፕሪቶሪያ የተነሳውን  የፀረ -ስደተኞች ተቃውሞ ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስና ውሃ መርጨቱ  ተመልክቷል ።

በዕለቱ በፕሪቶሪያ ከተማ  የውጭ ዜጎችና  የደቡብ አፍሪካ  ተወላጆች  ዱላዎችን ፣ ድንጋዮችንና የስለት መሣሪያዎችን በመያዝ  በተፋጠጡበት  ወቅት  ፖሊስ በመሃል በመግባት የመከላከል ሥራ ከማከናወኑም በላይ  የፖሊስ ሄሊኮፕተሮች በከተዋማ ሲያንዣብቡ ነበር ።

ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ከሰልፉ በፊት  ህዝቡ  እንዲረጋጋ ጥሪ አቅርበው ነበር ።  በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ  የሚደርሰውን ጥቃትና ማስፈራራትም   ፕሬዚደንት ዙማ አውግዘዋል ።  

ብዙ የደቡብ አፍሪካ  ተወላጆች የውጭ አገር ስደተኞች የደቡብ አፍሪካ ተወላጆችን  የሥራ ዕድል ወስደዋል ብለው ያምናሉ ።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ  በፕሪቶቲያ አካባቢ በጆሃንሰበርግ ደቡብ አፍሪካውያን ተደራጅተው   በሶማሊያውያን ፣ በፓኪስታናውያንና የናይጄሪያውያን ሱቆችን አጥቅተዋል ዘርፋም አካሄደዋል ።

ፕሬዚዳንት ዙማ  በተጨማሪም  በደቡብ አፍሪካ  የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ህግ አክባሪና ለአገሪቱም  ኢኮኖሚ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ በመሆኑ ሊከነሩ ይገባል ብለዋል ።

“ ሁሉም የውጭ ዜጎች   ህገ ወጥ የሰውና አዘዋዋሪዎችና ዕፅ ነጋዴዎች አይደሉም ። ይህን አይነት ወንጀል የሚሠሩትን ከንጹሃኑ መለየት ይገባል ” ብለዋል ፕሬዚደንቱ ።

የደቡብ አፍሪካ  የአገር ውስጥ  ሚኒስትር በበኩላቸው ድርጅቶች ዶክመንት የሌላቸውን ሠራተኞች  መቅጠራቸውን እንመረምራለን ብለዋል ።

ከተቃውሞ ጀርባ የሚገኙት የማሜሎዲ ኮንሰርንድ ሬዚደንት ቡድን እንደገለጸው ስደተኞች የዜጎችን የሥራ ድርሻ እየወሰዱ መሆናቸውንና በሴተኛአዳሪናትና በዕፅ ንግድ ላይ ተሠማርተዋል ይላሉ ።

በደቡብ አፍሪካ እኤአ  በ2008  የጸረ ስደተኞች  ተቃውሞ  የተነሳ ሲሆን  ከ60 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል ።