በሶማሊያ የአልሸባብ አመራር  ሁሴን ሳላህ ሙክታር  እጁን ሰጠ

 

በሶማሊያ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አመራር አንዱ የሆነው ሁሴን ሳላህ ሙክታር ለሀገሪቱ ጦር እጁን መስጠቱን በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል አሚሶም አስታወቀ፡፡

አሚሶምና አዲሱ ተመራጭየሶማያ ፕሬዝዳንት  በቅርቡ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት አዲሲቷን ሶማሊያን በመገንባት ሂደት ውስጥ ትጥቃቸውን በመፍታትእና ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ነበር ፡፡

የአመራር አባሉ ሁሴን ሳላህ ሙክታር እጅ መስጠቱም የዚሁ ጥሪ መላሽ እንደሆነ አሚሶምን ጠቅሶ  የኬንያው  ስታንዳርድ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡