በሶማልያ አስር የባህር ላይ ወንበዴዎች ተያዙ

 

የሶማልያ ፀጥታ ኃይላት ኧል-ካዉሳር የተሰኘች የሕንድ የእቃ ማመላለሻ መርከብ አግተዉ የነበሩ የባህር ላይ ወንበዴዎችን ያዙ።

ከዚህ ወር መጀመርያ አንስቶ በባህር ላይ ወንበዴዎች ታግታ የቆየችዉን መርከብና የመርከብዋ ሠራተኞች ትናንት ሰኞ የአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ታድገዋቸዋል ።

 የጋላካዮ ከተማ ከንቲባ እንደገለጹት 10 የባህር ላይ ወንበዴዎች እጃቸዉን የሰጡ ሲሆን ሦስቱ አጋቾች ደግሞ ማምለጣቸዉ ተዘግቧል።

የፀጥታ ኃይሎች ፣ ምግብና የመጠጥ ዉኃ ለአጋቾች እንዳይገባ ከመከልከል በተጨማሪ የሦስቱን አጋቾች ወላጆች መርከቧ ድረስ በማምጣት ሰዎቹንና መርከቧን እንዲለቁ ለማስገደድ ሞክረው ነበር ።ምንጭ -www.DW.com