በደቡብ አፍሪቃ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ጠየቁ

በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ሰባት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የጠሩት የተቃዉሞ ሰልፍ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ጠየቁ።

ተቃዋሚዎቹ ባወጡት መግለጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተለያዩ አቋሞችን የሚያራምዱ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ የሚከተሉት መንገድ ሃገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ትርምስ ከማምራቱ በፊት ስልጣን ይልቀቁ ብለዋል።

በ 10 ሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎች የታጀበዉ የተቃዉሞ ሰልፍ የተካሄደዉ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ፤ ትናንት 75ኛ የልደት በዓላቸዉን በሚያከብሩበት እለት ነዉ።

የአፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ ደጋፊዎች ለፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ 75 ኛ የልደት በዓል ሽር ጉዳድ ሲሉ ተቃዋሚዎች የሲቢክ ማህበራትና ደጋፊዎቻቸዉ መነሻዉን የመንግሥቱ መቀመጫ ከሆነዉ ፕሪቶርያ ቸርች ስኩየር አደባባይ በመሰባሰብ ተቃዉሞአቸዉን አሰምተዋል።

ምንጭ -www.dw.com