ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ሊያቀኑ ነው

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ሊያቀኑ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከሐምሌ 21 አንስቶ በአስመራ የሦስት ቀናት ቆይታ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ወደ  አስመራ የሚያቀኑት በኤርትራው አቻቸው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ነው ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር ወደ አሥመራ እንደሚያቀኑ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር መልዕክታቸው አስታውቀዋል፡፡