ሶማሊያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ብርጋዴር ጀነራል ሾመች

የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ካይር ኮሎኔል ዛኪያ ሁሴንን በትናንትናው እለት በብርጋዴር ጀነራልነት ማእረግ ሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞቃድሾ በሚገኛ በካህያ አጠቃላይ የፖሊስ ማሰልጠኛ ላይ በተደረገው የሹመት ስነ ስርዓት ላይ የሴቶች ሚና እውቅና ሊሰጠወው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ባከናወኗቸው ልክ እውቅና የመሰጠት መብታቸው ሊጠበቅ ይገባዋል ያ ካልሆነ ግን ከጎረቤት ሃገራት ጋር ልንወዳደር አንችልም ብለዋል፡፡

የሶማሊያ ሴቶች ከዚህ በላይ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግም እንዲፎካከሩ አበረታታለሁ ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ካይር ተናግረዋል፡፡

በበዓለ ሲመቱ ላይ ሌሎች ፖሊስ አባላትም ተሹመዋል፡፡ ( ምንጭ:የዘ ኢስት አፍሪካ )