ኤርትራና ጅቡቲ በመካከላቸው ያለውን ውዝግብ እንዲፈታ ኢትዮጵያ ትሠራለች

የኤርትራ እና የጅቡቲ መንግስታት በመካከላቸው ያለውን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸው ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ኢትዮጵያ በትጋት ትሰራለች ሲል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የመሩት የልዑክ ቡድን “በአፍሪካ ቀንድ የሠላም ዘመኑ ይብሰር” በሚል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው አማካኝነት ለጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ያስተላለፉትን መልዕክትም አቅርበዋል፡፡

የጅቡቲው መሪ ሀገራቸው ከኤርትራ ጋር ያላትን ውዝግብ ለመፍታትና ለዓመታት የተቋረጠውን ግንኙነት ለማደስ ዝግጁ መሆኗን ለልዑካን ቡድኑ ገልጸዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ባደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ (ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት )