ህብረቱ ለሰላም ፈንዱ መዋጮ በማይከፍሉ አገራት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ወሰነ

የአፍሪካ ህብረት ለሰላም ፈንዱ የሚጠበቅባቸውን መዋጮ በማይከፍሉ ሀገራት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ወሳኔ በመሳለፍ ተጠናቀቀ ።

በአዲስ አበባ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ህብረት 11ኛው ልዩ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎች በመሳለፍ ስብሰባውን አጠናቋል ።        

በስብሰባ መሪዎቹ የሚጠበቀባቸውን የገንዝብ መዋጮ ባላዋጡ ሀገራት ላይ ማዕቅብ ለመጣል የሚያስችል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ማሻሻያንም በጥናት ላይ ተመሥርቶ ተግባራዊ  ለማድረግም  ወስኗል።

በመሪዎቹ ውሳኔ መሠረት ለተከታተይ ስድስት ወራት ከሚጠብቅባቸው መዋጮ ግማሹንና ከዛ በላይ መክፈል ባልቻሉ ሀገራት ላይ ማዕቀብ ይጣልባቸዋል።

ማዕቀቦችም የማስጠንቀቂያ፣ የአጭር ጊዜ እና የረዥም ጊዜ ተብለው  በሶስት ምዕራፍ ተከፋፍለው የሚተገበሩ ናቸው።

በማስጠንቀቂያ ማዕቀብ መዋጯቸውን መክፈል ያልቻሉ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ሃሳብ የመሥጠት(የመናገር) መብታቸው ላይ እገዳ ይጣልባቸዋል።

በመካከለኛው ምዕራፍ ማስጠንቀቂያ ደግሞ፥  በህብረቱ ሥር  ከሚገኙ ተቋማት አባልነት፣ የተቋማት መቀመጫ የመሆን ፣ዜጎቻቸው ከአፍሪካ ሀገራት ምርጫ ታዛቢነት  እና ዜጎቻቸው ከህብረቱ የተለያዩ ሥራ መደቦች የመቅጠር እገዳ እንደሚጣልባቸው ተመልክቷል።

የረዠም ጊዜ ማዕቀብ የሚጣልባቸው ሀገራት፥ ከህብረቱ አባልነት እስከ መታደግ ድረስ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ከህብረቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ እስካሁን ተገቢውን መዋጮ እያዋጡ ያሉ ሀገራት አትዮጵያን ጨምሮ  አስራ አንድ ናቸው ተብሏል።

ሌላው የህብረቱ መሪዎች ውሳኔ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንን ዳግም ማደረጃት ሲሆን፥ የዚህ  የሪፎርም ሃሳብ በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዲከናወን ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ሪፎርሙ፥ስምንት የነበረውን  ኮሚሽን ቁጥር ወደ ስድስት መቀነስ፣ የህብረቱ ኮሚሽነር ወንድ ከሆኑ ምክትላቸው ሴት እንዲሆኑ ፣ኮሚሽነሩን የሚያግዙ ዋና ፅሃፊ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ብቃትን መሰረት ባደረገ መስፈረት ተወዳድረው እንዲቀጠሩም መሪዎቹ ወስነዋል።

የህብረቱ ሪፎርም ውሳኔም ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ የሚተገበር መሆኑ ተነግሯል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)