ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አልበሽር በወንጀለኝነት መጠየቅ አለባቸው አለ

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሃስን አልበሽር በወንጀለኝነት መጠየቅ አለባቸው ብሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንቱ በሱዳናዊያን ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ግፍ አድርሰዋል ሲል ወንጅሏል፡፡

በስልጣን ዘመናቸው ወንጀል ሰርተዋል ያላቸዉን አካላት የሚከሰው ዓለም አቀፉ የጦር ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ አልበሽር በስልጣን ዘመናቸው ወንጀል ፈፅመዋል በዚህም መጠየቅ አለባቸው ሲል አስታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱን ከስልጣን አስወግዶ ስልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊው መንግስት ፕዝዳንቱን ለክስ እንዲያቀርብ አበረታታለሁ ሲል ነው ፍርድ ቤቱ የገለፀው፡፡

ፋቱ ቦንሱዳ የተባበሩሩት መንግስታት ድርጅት የደህንነት ሃላፊ ፋቱ ቦንሱዳ  እንደገለፁት ፕሬዝዳንት አለበሽር በሱዳናዊያን ላይ ከፈፀሙት ግፍ እና ጭቆናም በተጨማሪ በዳርፉር ለዘመናት ተቀጣጥሎ ለሚገኘው ጦርነት ተጠያቂ ናቸው ሲሉ መናገራቸዉን የወጣው ዘገባ አመላክቷል፡፡

እንደ ቦንሱዳ ገለፃ ፕሬዝዳንቱ በስልጣን ዘመናቸው በፈፀሙት ግፍ ለሱዳናዊያን ክፍያ የሚከፈልበት እና ፍትህን የሚያገኙብት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡

ግዜው አሁን የሱዳናዊያን ነው ያሉት የደህንነት ኃላፊዋ አልበሽር በስልጣን ዘመናቸው ስለፈፀሙት በደሎች የጦር ፍርድ ቤቱ አጠቃላይ ሪፖርቱን እንደሚያቀርብ ጠቅሰዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የጦር ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት አሞራ ሀሰን አልበሽር ለበርካታ ንፁሃን ዜጎች ሞት ተጠያቂ ከመሆናቸዉም በተጫመሪ በፆታ ትንኮሳም የሚጠየቁ ናቸው ነው የሚለው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደህንነት ሃላፊዋ  ቦንሱዳ በሱዳን የህግ የበላይነት እና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የሚችሉትን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉም ገልጸዋል፡፡/አልጀዚራ/