የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት እና ተቃዋሚ ሃይሎች ስልጣን ለመጋራት የሚያስችላቸው ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

የአፍሪካ ህብረት ዲፕሎማት እንዳስታወቁት ሁለቱም ሃይሎች ስልጣን ለመጋራት የሚያስችላቸው ስምምነት ዛሬ ይፈራረማሉ፡፡

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በአገሪቱ የተሞከረውን መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን ባሳወቀበት ሰዓታት ልዩነት የአፍሪካ ህብረት ዲፕሎማት መሃሙድ አል ሃሰን ላባት ሁለቱም ሃይሎች ስምምነት ኢንደሚፈራረሙ አስታውቀዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት በሃገሪቱ የጋራ ሉዓላዊ ምክር ቤት በመመስረት ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ከሁለቱም ሃይሎች በተውጣጣ አስተዳደር ትመራለች፡፡

ስምምነቱም በአገሪቱ ላጋጠመው አለመረጋጋት ጥሩ መፍትሄ ሆኖ ቀርቧል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል ጄኔራል ጀማል ኦማር በአገሪቱ መፈንቅለ መንግስት ተሞክሮ እንደ ከሸፈ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ 16 ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀው ነበር፡፡

(ምንጭ፡- ሲጂቲኤን )