ሱዳን አምስት ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ አመፅ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጋ አድርጋለች፡፡
የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ሰኞ እለት ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተቃዋሚዎች መሰባሰብ እንደጀመሩ ነው የተነገረው፡፡
በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ባለፈው ሰኞ ከተገደሉት አምስት ወጣቶች መካከል አራቱ ተማሪዎች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
በተማረዎች መገደል የተቆጡት ተማሪዎችም ዩኒፎርሞቻቸውን እንደለበሱ በካርቱምና በሌሎች ከተሞች ለተቃውሞ ወጥተዋል፡፡
የሽግግር ምክር ቤቱም ተቃውሞችን ለመቆጣጠርም መዋለ ህፃናት፣ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እዲዘጉ መወሱን ሱና የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
ከተገደሉት ተማሪዎች በተጨማሪ 62 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
(ምንጭ፦ቢቢሲ)