የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት አልበሽር ከሳዑዲ አረቢያ 90 ሚሊየን ዶላር መቀበላቸውን አመኑ

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሳን አልበሽር ከሳዑዲ አረቢያ 90 ሚሊየን ዶላር መቀበላቸውን አምነዋል።

በህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ፣ በሙስናና የተለያዩ ስጦታዎችን ያለ አግባብ በመቀበል ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል ።

የ75 ዓመቱ የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሳን አልበሽር ከሳዑዲ አረቢያ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ እንደተቀበሉ ማመናቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

አልበሽር 90 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከሳዑዲ ልዑል ብርጋዴር ጀነራል አህመድ አሊ በጥሬ ገንዘብ መቀበላቸው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ በመኖሪያ ቤታቸው በተደረገ ፍተሻ 7 ሚሊየን ዩሮ፣ የአሜሪካ ዶላሮችና የሱዳን ፓውንዶች እንደተገኙባቸው ዘገባው አመልክቷል።

በተጨማሪም ኦማር ሀሰን አልበሽር በ2015 ህይወታቸው ካለፈው ከከቀድሞው የሳዑዲ ንጉስ አብደላህ 65 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መቀበላቸውን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።

ምንጭ፦አልጀዚራ