ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከሰባት ወራት በኋላ አዲስ ካቢኔ አቋቋመች

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አዲሷን ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሲሼኬዲ ወደ ስልጣን ካመጣች ከሰባት ወራት በኋላ የጥምር መንግስት ካቢኔ አቋቁማለች፡፡

ሀገሪቷ በ1960 ከቤልጅየም ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ህዳር ወር ላይ በተካሄደው ምርጫ ለማድረግ በቅታለች።

አዲሱ ፕሬዝዳንት ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪስተር ኢሉንጋ ለኤኤፍፒ፣ በመጨረሻም መንግስት እዚህ ተገኝቷል፤ ፕሬዝዳንቱ በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፣ በቅርቡም ስራው ይጀመራል ሲሉ ተናግረዋል።

(ምንጭ፡-ቢቢሲ)