በግብፅ የ3 ሺህ አመት ያለው የመቃብር ሰፍራ ተገኘ

በግብጽ ከ3000ሺ  ዓመት በላይ ያሰቆጠረ የመቃብር ሰፍራ መገኘቱን  የሰነ ምድር ተመራማሪዎች   አስታወቁ፡፡

በፖለቴካ አለመረጋጋት ውሰጥ ለምትገኘው ግብጽ ይህ የጥንታዊ ቅርሰ መገኘት ጎብኝዎች ወደ ሀገሪቱ ዳግም እንዲተሙ እና የቱሪዝም ንግዱ እንዲንሰራራ ተሰፋ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

የመቃብር ሰፍራው በናይል አቅራቢያ በምትገኝው ሉክሰር ከተማ አካባቢ እንደተገኝ ነው የተነገረው ፡፡

የመቃብር ስፍራው አራት መአዘን አዳራሽ መሳይ ሲሆን መተላለፊያ እና የተለያዮ ክፍሎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡

 ተመራማሪዎቹ  እንደሚሉት በመቃብር ሰፍራው በአንደኛው ክፍል ውሰጥ አሻንጉሊቶች የእንጨት ጭንብሎች እና የተለያዮ ጥንታዊ ቅርሶች መገኝታቸው ተገልጿል፡፡

ቁፋሮው በሌላኛው ክፍል ውስጥም  እንደቀጠለ ነው የተነገረው፡፡

 ከክርሰቶስ ልደት በፊት ከ664 እሰከ 610 ዓመተ ዓለም ይገዛ የነበረው ንጉሰ ፓሰማቲክ አንደኛ እንደሆነ የተነገረለት 8 ሜትር ርዝመት ያለው ሃውልት በቁፋሮ በካይሮ   መገኝቱንም አሰታውሰዋል፡፡

የግብጽ ቱሪዝም ልማት ባለሰልጣን ኃላፊ የሆኑት ሂሻም ኤል ዲሚትሪ እንዳሉት "የዚህ ጥንታዊ ቅርስ መገኘት ለግብጽ ትልቅ ዜና ነው የቱሪዝም ዘርፉን  ከማበረታታት  ፣ ከማሳደግ እና የጎብኝው ቁጥር ከመጨመር አንጻር ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡"