በኡጋንዳ ካንሰር በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ በሽታ እየሆነ መምጣቱ የሀገሪቷን መንግስት አሳስቧል ተባለ

በኡጋንዳ የካንሰር ህምም በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ በሽታ እየሆነ መምጣቱ የሀገሪቷን መንግስት አሳስቧል እየተባለ ይገኛል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመላው ዓለም ለሞት መንስዔ ከሆኑት ነገሮች አንዱ የካንሰር በሽታ ሆኗል በአውሮፓዊያኑ 2012 8 ነጥብ 2 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች በካንሰር በሽታ  ሲሞቱ በየዓመቱም  171 ሺህ አዲስ የካንሰር በሽታዎች ሪፖርት ይደረጋሉ ፡፡

በሚቀጥሉት ሁለት አሥርተ ዓመታት እነዚህ አዳዲስ የካንሰር ህምም ውጤቶች 70 በመቶ እንደሚጨምሩ ይገመታል ፡፡

የህዝብ ጤና ጥበቃ ባለሙያ የሆኑት  ዶክተር ዴኒስ ቡዌምቦ  እንደሚሉት በጣም የተለመዱ የካንሰር ዓይነቶች ከኤችአይቪ / ኤድስ ጋር የሚዛመዱት የፕሮስቴት፣ የማህጸን ጫፍ፣ የጡት ካንሰር፣ ቧንቧ እና ካፖሲ ሳርኮማ ናቸው ፡፡

አክለውም  በጣም የተለመዱት የካንሰር ዓይነቶች በሰውነት ውስጥ የሚገኙት የፕሮስቴት፣ የቆዳ ካንሰር፣ የመተንፈሻ ቱቦዎች፣ የነጭ የደም ሴሎች ካንሰር እና የጉበት ካንሰር ሲሆኑ  ለሴቶች የጡት ካንሰር ነው ብለዋል ፡፡

ዶክተር ቡዋምቦ  በኡጋንዳ  በካንሰር ህመሞች  በሆኑት  የፕሮስቴት፣ የደም ካንሰር  እና የካፖሲ ሳርኮማ ካንሰር በቀዳሚነት ገዳይ በሽታ  መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ 2012 ይፋ ያደረገው መረጃ  አረጋግጧል ፡፡

በካምፓላ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም የሆኑት ዶክተር ሙሳ ግራኩዋንስ በተለመደው የጡት ካንሰር ህመም እና የማኅጸን በር ካንሰር ቁጥራቸው በርከት ያሉ  ታማሚዎች  በሆስፒታላችን  ይገኛሉ  በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት የታማሚዎቹ ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል የሚለው ስጋታችን ነው ብለዋል ፡፡  

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኡጋንዳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው  የማኅጸን ካንሰር ህሙማን የሚገኙባት  መሆኑዋም እየተነገረ ይገኛል፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በዋነኛነት  የማኅጸን ካንሰር ትልቁ ስጋት ነውም ተብለዋል ፡፡

ዶክተር ቡዌምቦ እንደሚሉት እስካሁን በተደረጉ ጥናቶች በኡጋንዳ የሚገኙ  የካንሰር ህሙማን በህይወት የመቆየት እድላቸው ዝቅተኛ ነው ፡፡ (ምንጭ፤ኒውስ 24)