በኬንያ በተከሰተው ድርቅ ከአንድ ሚልዮን በላይ ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ

በኬንያ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከአንድ ሚልዮን በላይ ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ፡፡

በተለይም በሰሜናዊ የኬንያ ክፍል የሚኖሩ አርብቶአደሮች በድርቁ ምክንያት ለስደት እና ለግጭት መዳጋቸው ተገልጿል፡፡

አና ሊሳንጅሬ በሰሜን ኬንያ በአርብቶ አደርነት የሚተዳደሩ ኬንያዊት ሲሆኑ፣ በአካባቢያቸው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ግጦሽ እና ውሃ በመጥፋቱ  ከነቤተሰባቸው ለመሰደድ ተገደናል ብለዋል፡፡

ለሚያረቧቸው እንስሳት የሚሆን ግጦሽና ዉሃ ለማግኘትም የአንድ ቀን ጉዞ እንደሚያደርጉ ነው የገለጹት፡፡

በሰሜናዊው ኬንያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እረኞች ለከብቶቻቸው የሚሆን ግጦሽና ዉሃን ለማግኘት ማራላል ወደተባለች አካባቢ እና ወደ ሌሉችም ስፍራዎች ይሰደዳሉ፡፡

በሀገሪቱ እየተከሰተ ባለው ተደጋጋሚ ድርቅ ምክንያትም በእረኞች እና በአካባቢው ተወላጆች መካከል ግጭቶች ይነሳሉ ተብሏል፡፡

እንደ የአልጀዚራዋ ካትሪን ሶል መረጃ በአካባቢው የሚነሱ ግጭቶች መንስኤያቸው ቀላል ቢሆንም የበርካቶችን ህይወት እስከመቅጠፍ ይደርሳል፡፡

እነዚህ በኬንያ ሳምቡሩ በተባለች ቦታ የሚኖሩ ሽማግሌዎችና የጎሳ አባላት ናቸው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት በተከሰተው ችግር ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት ፀብ እና መፍትሔ ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

በኬንያ እንዲህ ዓይነቱ ድርቅ ተከስቶ ሚልየኖችን ለርሃብ ሲያጋልጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የዛሬ ሁለት ዓመት በገጠማት ድርቅ ምክንያት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ማወጇ አይዘነጋም፡፡ (ምንጭ፡-አልጀዚራ)