በታንዛኒያ ያላገቡ ሴቶችን ከመታለል ለመታደግ ያገቡ ወንዶች የመረጃ ቋት እንዲቋቋም ሃሳብ ቀረበ

በታንዛኒያ የዳሬሰላም ገዢ ያላገቡ ሴቶችን ከመታለል ለመታደግ ያገቡ ወንዶች የመረጃ ቋት እንዲቋቋም ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

በአጭበርባሪ ባለትዳር ወንዶች የሚሠቃዩ ሴቶችን ጉዳት መቀነስን ዓላማ ያደረገ እንደሆነ  ገዢው ፖል ማኮንዳ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመትበርካታ ያላገቡ ሴቶች ወደ ቢሯቸው በመጡበት ወቅት የችግሩን ስፋት በመረዳት  ሀሳቡ እንደመጣላቸው ፖል ማኮንዳ ገልጸዋል፡፡

ሚስተር ማኮንዳ ስለ አዲሱ የመፍትሄ እቅድ  ሂደት ምንም ዓይነት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡

ገዢው አወዛጋቢ መግለጫዎችን በመስጠት እንደሚታወቁ በዘገባው ያስታወሰው ቢቢሲ ነው፡፡