የቀድሞ ዝምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞ የዝምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ለሶስት አስር አመታት ዝምባቢዌን የመሩት ሙጋቤ፣ በፈረንጆቹ ህዳር 2017 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ነው ከስልጣናቸው የተነሱት፡፡

ሙጋቤ በሕመም ላይ ቆይተው ማረፋቸውንም ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል፡፡

የዝምባብዌ የትምህርት ሚኒስትር ፋድዛይ ማሂር እረፍታቸውን አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው በኩል የነፍስ ይማር መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ (ምንጭ፡-ቢቢሲ)