በሶማሊያ 2 ሚሊየን ሰዎች ለርሃብ መጋለጣቸውን ተመድ አስታወቀ

በሶማሊያ 2 ሚሊየን ሰዎች ለርሃብ አደጋ መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሃፊ ማርክ ሎውኮክ ከሶማሊያ የሁለት ቀናት ጉብኝት በኋላ 2 ሚሊየን ሰዎች ለርሃብ አደጋ መጋለጣቸውን አስውቀዋል፡፡

ባለፉት ተከታታይ አመታት ድርቅ ክፉኛ በተደጋጋሚ በጎበኛት ሶማሊያ በሚቀጥለው ወር 6 ሚሊየን ሰዎች የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ አሃዝ አንድ ሶስተኛ ያህሉ ለከፋ የምግብ እጥረት ችግር የሚጋለጥ እንደሆነም ነው ያስጠነቀቁት፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ