ሩዋንዳ ከሊቢያ የመጀመሪያዎቹን 66 ስደተኞች ተቀበለች

በሩዋንዳ መንግሥት፣ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና በአፍሪካ ህብረት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ነው የመጀመሪያው የስደተኞች ቡድን ሩዋንዳ የገባው፡፡

ሩዋንዳ አውሮፓ ለመድረስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ እና በሊቢያ በአደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ከ500 በላይ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማምታለች፡፡

ከእነዚህ ውስጥ ታዲያ 66ቱ ስደተኞች ሩዋንዳ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ለሩዋንዳ ህዝብና መንግስት ልዩ ምስጋና ማቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሩዋንዳ ከደረሱት ስደተኞች ከፊሉ የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች ሲሆኑ ከመካከላቸው አንዲት የሁለት ወር ጨቅላ እንዲሁም ብቸኛ ሕፃናት እና ሴቶች ይገኙባቸዋል፡፡