የጃፓን የውጭ ንግድ ለአምስተኛ ተከታታይ ወራት አሽቆለቆለ

የጃፓን የውጭ ንግድ ለአምስተኛ ተከታታይ ወራት ማሽቆለቆሉን የሃገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይፋ የሆነው መረጃ እንዳመለከተው ባለፈው የፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር የጃፓን የውጭ ንግድ 2 ነጥብ 4 በመቶ ቀንሷል፡፡

ይህም በመጋቢት ወር ከተመዘገበው ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ላለፉት አምስት ተከታታይ ወራት  ማሽቆልቆሉ ነው የተነገረው፡፡

ሃገሪቱ ከፍተኛ ትርፍ ከምታገኝባቸው የንግድ ዘርፎች አንዱ የጃፓን-ቻይና የንግድ መርከብ አገልግሎት ሲሆን በዚሁ ዘርፍ 6 ነጥብ 3 በመቶ ማሽቆልቆል ተመዝግቧል፡፡

በተጨማሪም ጃፓን ለአውሮፓ ገበያ በምታቀርባቸው ምርቶች ላይ የ 3 በመቶ ቅነሳ ተመዝግቧል፡፡

ምንም እንኳ የቻይና እና አውሮፓ የውጭ ንግዷ ቢያሽቆለቁልም የአሜሪካ የውጭ ንግዷ ግን በ9 ነጥብ 6 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡

የሃገሪቱ የውጭ ንግድ ላይ ማሽቆልቆል ቢመዘገብም በመጀመሪያው ሩብ አመት የጃፓን ጂዲፒ በ2 ነጥብ 1 በመቶ እድገት አሳይቷል/ሲጂቲኤን/