አሜሪካን በሜክሲኮ የጣለችውን የ5% ታሪፍ ለመቀነስ ምክክር ያስፈልጋል -ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሜክሲኮ ባልስልጣናት ጋር ባደረጉት ቆይታ ዋሺንግተን ከሜክሲኮ ከምታስገባቸው ምርቶች የአምስት በመቶ ታሪፍ ለመቀነስ ዳግም ምክክር እንደሚያስፈልግ ተናገሩ፡፡

ትላንት በተደረገው ድርድር በተወሰነ መልኩ ስምምነት ላይ ቢደረስም ቀጣይ ውይይቶች እንደሚደረጉ ትራምፕ ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ ከሜክሲኮው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርሲሎ ኢብራድና የልዑክ ቡድኑ ጋር በዋይታ ሀውስ ለ1፤30 ያደረጉት ድርድር ያለስምምነት መቋጫውን አግኝቷል፡፡

የሜክሲኮው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራድ እንዳስረዱትም ጥሩ የተባለ ውይይት አድረገናል ቢሉም የታሪፍ ጉዳይ ግን አለመነሳቱን አልሸሸጉም፡፡ይልቁኑ የምክክሩ ትኩረት በፍልሰት ዙሪያ እንደነበርና ሜክሲኮ በመካከለኛው አሜሪካ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ድንበሯን ተሻግረው እንዳይገቡ ስለሚኖራት ሚና በስፋት መነጋገራቸውን አውስተዋል፡፡

ይህንኑ አስመልክቶም ሁለተኛውን ያለም ጦርነት ለመዘከር አውሮፓ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የፍልሰቱ ጉዳይ እልባት ካለገኘ የታሪፍ ውሳኔው እንደሚቀጥል በቲውት ገጻቸው አስነብብዋል፡፡ ይባሱኑ ከሜክሲኮ ከሚገቡ ተሸከርካሪ፤ የቢራ መጠጦች፤አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ በየወሩ አምስት በመቶ ታሪፍ እንሚጨመረ ማቀዳቸውን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሜክሲኮ ድንበሯን ተሸግረው የሚመጡባትን የውጪ ዜጎች እንዳስቆምላት በጥብቅ ቢሹም ሁኔታዎች ከዚህ በተቃራኒው እንደቀጠሉ ነው፡፡ አሜሪካ የሜክሲኮ ድብሯን በግንብ አጥር ለመገንባት ውጥን ቢያቀርቡም ከፓርቲያቸውና ከፋይናንስ ምንጮች አዎንታን ባለመግኘታቸው ተጨናግፏል፡፡

የነጩ ቤተመንግስት የንግድ ልውውጥ አማካሪ ፒተር ናቫሮ አስቀድሞ በድርድሩ ሁለቱ ወገኞች ሊቀራረቡ እንደሚችሉ አስረድተው የኘበረ ቢሆንም አሁን ባለው ምልኩ ግን የታሪፍ ድርድሩ ለውጥ እንዳላመጣ ለCNN ተናግረዋል፡፡አክለውም የትራምፕ ፍላጎት ሜክሲኮ ጥግኘነት ጠያቂዎችን እንዳስቀርላቸው ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው በማንሳት ከዚህ አኳያ የታሪፍ ውሳኔው ፍሬ አልባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬስ ማንዌል ሎፔስ ኦብራዶር ከሜሪካ ጋር በንግድ ልውውጥ ያለቸው ልዩነት እንዲፈታ ፍላጎት እንዳላቸው ይነገርላቸዋል፡፡  ምክኒያቱ ደግሞ በዋናነት እያሽቆለቆለ  የመጣውን የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ለመታደግ ሲሉ መሆኑን ተንታኖች ያነሳሉ፡፡ ትራምፕ አስቀድሞ የሚክሲኮን ድበር ለመዝጋት አስተላለፈው የነበረውን ውሳኔ መግታታቸው አሁን እየተደረገ ባለው ድርድር ቁርጥ ያለ አቋም ለመያዝ እንዳስገደዳቸው ተንታኞቹ አያይዘው ያነሳሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ልክ ከቻይና ጋር ለገቡበት የንግድ ጦርነት አይነት ምላሽ አንዳይሰጡ ስጋት ጭሯል፡፡