በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራንፕ 45ኛው ፕረዚዳንት ሆኑ

አዲሱ የአሜሪካን ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው 289 ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል ።

ሂላሪ ክሊንተን 218 የምርጫ ድምፆችን አግኝቷል ።

በአሜሪካ ህግ ፕረዚዳንት ለመሆን 270 ያህል የምርጫ ድምፆችን ማግኘት በቂ መሆኑ የሚታወቅ ነው ።

ሂላሪ ክሊንተን በቅድመ ምርጫ የብዙዎች ግምት የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ፕረዚደንት ይሆናሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሊሳካ አልቻለም ፡፡

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፐብሊካኖቹ 232 መቀመጫዎችን እንደዚሁም ደግሞ  ዲሞክራት ፓርቲ 173 መቀመጫዎችን አግኝተዋል።

በአገሪቱ ባሉት 100 የህግ መወሰኛ ምክር ቤት መቀመጫዎች  ውስጥ ሪፐብሊካን ፓርቲ 49 ፤ ዴሞክራት 45 መቀመጫዎችን ማግኘታቸው ተረጋግጧል ። 

ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው በማሸነፋቸው መላ ቤተሶቦቻቸውንና ደጋፊዎቻቸውን የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡

እንደዚሁም “የሁሉም አሜሪካዊ ፕሬዚዳንት እሆናለሁ ” ያሉት ዶናልድ ትራንፕ ፤ አሜሪካውያን አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት ጊዜ አሁን መሆኑን ነው ያስገነዘቡት  ።

ምርጫውን ካሸነፉ ሂላሪ በፈጸሙት የሙስና ወንጀል ችሎት አቋቋመው  ወደ ፍርድ እንደሚያቀርቧቸው ሲዝቱባቸው የነበሩት  ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ  ባንጻሩ ለሂላሪ ክሊንተን ምስጋናቸውን ነው ያቀረቡት ።

አዲሱ ፕረዚዳንት ትራንፕ አሜሪካ በርካታ ወዳጅ አገሮች ይኖራታል ብለው እንደሚጠብቁ ም ገልጸዋል፡፡

ሂላሪ ክሊንተንም የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት  እንዳስተላለፉላቸው የተነገረ ሲሆን ፤ሩስያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራትም ተመሳሳይ መልዕክት እየደረሳቸው ይገኛል ነው የተባለው ።

ቢሊየነሩ ዶናልድ ትራንፕ  “አሜሪካን ዳግም ታላቅ እናዳርጋታለን!” በሚል የመቋጪያ ንግግራቸው ይታወቃሉ ።