ትራምፕ በዚህ አላበቁም ለሽብር ስጋት ያሏቸዉ ሀገራት የይለፍ ወይም ቪዛ ፈቃድ ጥያቄ እንዲያዝ የሚያደርግ መመሪያም እያወጡ መሆኑ ተጠቆመ ።
ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት ስደተኞችን እንደማይቀበሉ እና በሕገወጥ የገቡትንም አባርራለሁ በማለት ዝተዉ ነበር።
ትራምፕ በዚህ አላበቁም ለሽብር ስጋት ካሏቸዉ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ ኢራን፣ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ እና የመን ለ30 ቀናት የይለፍ ወይም ቪዛ ፈቃድ ጥያቄ እንዲያዝ የሚያደርግ መመሪያም እያወጡ ነዉ።
በትናንታናዉ ዕለት ታዲያ ሕገወጥ ተሰዳጆች ይገቡበታል ያሉትን ከሜክሲኮ ጋር ሀገራቸዉን የሚያዋስነዉን የድንበር አካባቢ በግንብ ለማጠር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ዉሳኔያቸዉ ያስቆጣት ጎረቤት ሜክሲኮም እንደሚሉት የግንቡን ወጪ አልከፍልም ብላለች።
አዲሱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት የፎከሩትን ተግባራዊ ከማድረጋቸዉ አስቀድሞ ለጥቂት ወደ አሜሪካ የገቡ ተሰዳጆች መኖራቸዉን የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል-(ዶችዌለ)።