ጀርመን አዲስ ፕረዚዳንቷን መረጠች

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የጀርመን 12ኛው ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

በበርሊን ከተማ ትናንት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር 12ኛው የጀርመን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

ሽታይንማየር 931 ድምፅ በማግኘት ምርጫውን በመጀመሪያው ዙር አሸንፈዋል።

ምርጫውን በአንዱ ዙር ለማሸነፍ ተመራጩ 631 ድምፅ ማግኘት ይገባዋል።

ሶሻል ዴሞክራቱ  ሽታይንማየር በሌሎች የጀርመን የፖለቲካ ፖርቲዎች ገና ከምርጫው በፊት ድጋፍ አግኝተዋል።

በጀርመን ፕሬዚዳንቱን የሚመርጡት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ቡንደስታግ)ተመራጮች እና የጀርመን ግዛቶች ተወካዮች ናቸው።

ከእነዚህ መካከል ታዋቂ አርቲስቶች እና ስፖርተኞች ይገኙበታል።

እንደሚያሸንፉ ሲጠበቁ የነበሩት ሽታየንማየር ምርጫውን በደስታ ተቀብለዋል።

ወቅታዊው የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ የስልጣን ዘመን ከአምስት ዓመት በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓም ያበቃል።

የ 77 አመቱ ጋውክ በእድሜያቸው ምክንያት ዳግም ለምርጫ መወዳደር ሳይፈልጉ ቀርተዋል-(ዶችዌለ) ።