በሶሪያ በተካሄደ አየር ድብደባ በትንሹ 72 ሰዎች በመርዝ ጋዝ ሞቱ

 

በሶሪያ በካን ሼኩን ከተማ በመንግስት ወይም በሩሲያ የአየር ድብደባ መካሄዱን እና በጥቃቱ ዘጠኝ ህጻናትን ጨምሮ ከ72 ሰዎች በላይ በመርዝ ጋዝ መሞታቸውን የሶሪያ ተቃዋሚዎች አስታወቁ ፡፡

ከነዚሁም ውስጥ 20 ህጻናትና 17 ሴቶች መሆናውን ነው የተመለከተው ፡፡

በከተማው ትናንት በተካሄደው በዚሁ የአየር ጥቃት ተከትሎ አካባቢው ነዋሪዎች በጭሱ ምክንያት ታፍነው እራሳቸውን መሳታቸውን እና በአፋቸው በአረፋ ተደፍቆ መመልከቱን መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገ የመብት ተሟጋች ድርጅት ገልጿል፡፡

ደማስቆ እንደዚህ ያሉ መሳሪያዎችን እንደማትጠቀም የገለጸች ሲሆን ፤የሶሪያ ጦር ወዲያው በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን ማገኘት እንዳልተቻለ ነው የተመለከተው ፡፡

የሶሪያ ብሄራዊ አማጺያን ቡድን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፋጣኝ የመንግስታቱ ድርጅት ጸጥታ ምክርቤት ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቋል፡፡

እሁድ እለት ባለቤትነታቸው የሩሲያ ሳይሆኑ እንዳለቀሩ የሚገመቱ የጦር ጄቶች በሰሜናዊ ኢድሊብ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ባደረሱት ሶስት የአየር ጥቃቶች ቢያንስ አስር ሰዎች መቁሰላቸው እና የሆስፒታሉ ህንጻ መፍረሱ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡