ዩናይትድ ስቴትስ በሶሪያ ላይ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ሩሲያ የአሜሪካንን ድርጊት ክፉኛ አወገዘች፡፡
አሜሪካ በሶሪያ መንግስት ላይ ያካሄደችው የሚሳኤል ጥቃት የመጀመሪያው ቀጥታ ወታደራዊ ጣልቃ መግባቷን ያሳያል ነው የተባለው ፡፡
የፕሬዚዳንት ባሽር አል አሳድ መንግስትን የምትደግፈው ሩሲያ፥ የአሜሪካንን ድርጊት ከመኮነን ባለፈ በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ የሁለቱ ሀገራት የጦር ጄቶች የአየር ላይ ግጭትን እንዳያካሂዱ ገቡትን ስምምነት ሩሲያ መሰረዟን አስታውቃለች፡፡
አሜሪካ የተጠቀመችው ተወንጫፊ ክሩዝ ሚሳኤል ዝቅ ብሎ የሚጓዝ ሲሆን፥ በአየር መቃወሚያ ለማምከን አስቸጋሪ ነው፡፡
ሩሲያ የሶሪያን ከምድር ወደ አየር ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ስርአት በማሻሻል የሶሪያን የመከላከል አቅም ለማሳደግ ውጥን እንደላት እየተነገረ ነው፡፡
ሶሪያ በሶቬት ዘመን የነበራት ብሄራዊ አየር ኃይል ስርአት ጠንካራ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ጦርነት በአየር ላይ መከላከል አቅሟን እንዳዳከመው ይነገራል፡፡
ሩሲያ የተወሰኑ ዘመናዊ ከምድር ወደ አየር ተወንጫፊ የሚሳኤል የጦር መሳሪያዎች በሶሪያ አየር ኃይል ምድብ ይገኛሉ፡፡
የሩሲያ ወታደራዊ ቃለ አቀባይ ሜጀር ጀነራል ኢጎር ኮንሼንኮቭ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ አየር ላይ ጥቃቶች “እጅግ ዝቅተኛ “ ያውም ከ59 የሚሳኤል ጥቃቶች 23 ብቻ ናቸው ኢላማቸውን የሚመቱት ነው ያሉት፡:
የአሜሪካ ባካሄደችው የሚሳኤ ጥቃት የእቃ ማከማቻ መጋዝን ፣የማሰልጠኛ ህንጻ እና ለጥገና የቆሙ ሚግ-23 ጄቶች ማውደሟን የሩሲያ ጦርን ጠቅሶ ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡
የሶሪያ መንግስት በጥቃቱ ስድስት ወታደሮች መገዳለቸውን አስታውቋል (ኤፍ ቢ ሲ)፡፡