አሜሪካ ከዚህ ቀደም በጦርነት ላይ ተጠቅማ በማታውቀው ከባድ ቦምብ አፍጋኒስታን በሚገኘው የአይኤስ ይዞታ ላይ ጥቃት ፈጸመች ፡፡
የአሜሪካ ወታደራዊ ሀይል በአፍጋኒስታን እስላማዊ መንግስት ተብሎ በሚጠራው በአይኤስ የሽብር ቡድን ይዞታላይ አስር ኩንታል የሚመዝን ቦምብ ጥሏል ፡፡
"የሁሉም ቦምቦች እናት" በመባል የሚታወቀው የ ግዙፍ የጦር መሣሪያ ሲሆን አሜሪካ ከሜቼውም ጊዜ በላይ ጥቅም ላይ ከዋሉት ትልቁ የኒውከሌር መስል ቦንምብ ነው ፡፡
ከፔንታጎን እንደተገለፀው ቦንቡ የተጣለው በተዋጊ አውሮፕላኖች በአፍጋኒስታንና በናጋር አከባቢ በሚገኘው በአይኤስ የወታደሮች ካምፕነው ፡፡
በናጋር አከባቢ አቺን ግዛት የተጣለው ይህ ቦምብ ርዝመቱ 9 ሜትር ይረዝማል፡፡
ከዋይት ሀውስ ባለስልጣናት በቦምቡ የጠፋውን የአይኤስ ወታድር ቁትር ለመግለፅ ቢቆጠቡም' የሁሉም ቦምቦች እናት' 'ብዙ የአይኤስ ወታደሮችን እንደገደለ'ተነግሯል፡፡
የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ እንደገለፁት ቦንቡ ድብደባ ከመካሄዱ በፊት በቂ ጥናት ተካሂዶ የአይኤስ ወታደሮች በነፃነት የሚነቀሳቀሱ እና የአሜሪካን ወታደሮችና አጋዥ አካላትን ለማጥቃት የሚጠቀሙባቸውን ዋሻዎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ነው፡፡ ቃል አቀባዩ አክለውም በጥቃቱ ሰላማዊ ዜጎች እንዳይጎዱም ጥንቃቄ ተደርጓል፡፡
የአቺን አውራጃ ገዢ ኢስማዒል ሽናዋሪ ቢቢሲ እንደገለጹት በጥቃቱ አከባቢ ሰላማዊ ሰዎች እንደማይኖሩም ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ "ስኬታማ ሥራ ሰርተናል በመከላከያችን ኮርቻለው! " ሲሉ ተደምጠዋል ፡፡