ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራኑ አቻቸው ጋር ለመወያየት ፍቃደኛ እንደሆኑ ገለጹ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራኑ አቻቸው ሀሰን ሮሀኒ ጋር በሀገሪቱ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ዙሪያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመወያት ፍቃደኛ እንደሆኑ ገለፁ፡፡

አሜሪካ በዘመነ ኦባማ የፈረመችውን የ2015ቱን የኢራን የኒዩክሌር መርሀግብር ስምምነት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ መንበረ ስልጣን ሲመጡ ስምምነቱን በተደጋጋሚ ከመተቸታቸው ባለፍ እንደማይቀበሉትም አቋማቸውን ሲገልፁ መቆታቸው ይታወሳል፡፡

አሁን አልጀዚራ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2015ቱ ኢራን ኒዩክሌር ስምምነትን አስመልክቶ ከኢራኑ አቻቸው ሀሰን ሮሀኒ ጋር ለመምከር እንደተዘጋጁ መናገራቸውን ነው፡፡ለዚህ ውይይት ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ እንደማያስፈልግም ነው ገለፁት፡፡

የኢራን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከእኛ ጋር ለመወያት ፍቃደኛ ከሆኑ ውይይቱ አሜሪካን ወጥታበት ከነበረው የ2015ቱ የኢራን ኒዩክሌር ስምምነት የሚመልስ መሆን ይገባዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ የአለም ሀያላን ፈረንሳይ፣ብሪታኒያ፣ሩሲያ፣ጀርመን፣ ቻይናና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከፈረሙት የኢራን የኒዩክሌር ስምምነት ሀገራቸውን ከማስወጣታቸው ባለፍ በሀገሪቱ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦች እንዲጣሉባት በተመድ በኩል ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

አሁን ግን ትራምፕ  በኢራን ኒዩክሌር ግንባታ ዙሪያ ወደ ድርድር የተመለሱ ይመስላሉ፡፡ለዚህ ማሳያቸው ደግሞ በዋይት ሀውስ ከጣሊያኑ ጠ/ሚኒስትር ጉስስፒ ኮንቴ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከኢራን ጋር ለመደራደርና ለመወያት ፍቃደኛ መሆናቸውን ለዋሽንግተን ፖስት ገልፀዋል፡፡

በዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቲዩተር ገፃቸው ላይም እንዳሰፈሩት ከሆነ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሀኒንም ሆኑ ኢራናዊያንና  ለማግኘትና ከእሳቸው ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነኝ እርሳቸው ዝግጁና ፍቃደኛ ከሆኑ  ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሁን የሰጡት አሰስተያትና መግለጫ ተከትሎ አሜሪካና ፕሬዝዳንት ትራምፕ  ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ከኢራን ኒዩክሌር ስምምነት ያፈነገጡበትን ውሳኔ ለመቀየር የሚስችል እና በኢራን ላይ ተጥለው የቆዩትን ማዕቀቦች እንዲነሱ በር የሚከፍት ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታገኞች አስተያየታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ባሳለፍናቸው ጊዚያት የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሃኒ  የተለያዩ የውይይት አማራጮችን ስይቀበሉ መቆየታቸውንም ፕሬዝዳንት ትራምፕ የተቀሱ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ቁም ነገር ነው ብለዋል፡፡ 

የፕሬዚዳንት ሀሰን ሮሀኒ አማካሪ የሆኑት ሀሚድ አቡታላቢ በበኩላቸው አሁን ላይ ኢራን ቁጣዋን በማቀዝቀዝ ማንኛውንም ውይይት ከአሜሪካ ጋር ማድረግ የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስከብርና አሜሪካን እንደገና ወደ ስምምነቱ ለመመለስ የሚያስችል እድል እንደሚፈጥር ነው የገለፁት፡፡

ከወራት እድሜ  በፊት ኢራን እንደ አውሮፓዎያኑ ዘመን ቀመር በ 2015 ከአሜሪካ፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሩሲያ፣ ቻይና እና የአውሮፓ ህብረት ጋር የተስማማችውን ውል አሜሪካ ትታ የወጣች መሆኑን ተከትሎ በተለይ ኢራን ነዳጅ አቅርቦቷን በማቆም የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ አሜሪካም ዋጋ ትከፍላለች ማለቷ አይዘነጋም፡፡

አሜሪካም ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሀገራትን ከኢራን የሚያስገቡትን የነዳጅ ምርት ማቋረጥ እንዳለባቸው ጫና ስታደረግ ብትቆይም ያሰበችው አልሆነላትም፡፡

ኢራን በበኩሏ የነዳጅ ምርቶቸቿን ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንዳትችል ከተደረገች በቀጠናው ያለውን የነዳጅ ምርት እንቅስቃሴ የምታግድ መሆኑን ስትገልፅ ቆይታለች፡፡

የሁለቱ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች የቃላት ጦርነት ሲለዋዎጡ የነበረ ሲሆን፥ አሁን ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራኑ አቻቸው ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመገናኘት ፍላጎት ያላቸው መሆኑ መግለፃቸው ሁለቱ ሀገራት ከተካረረ ፖለቲካ እንዲወጡ ያደርጋቸዋልም ተብሏል፡፡

ቴህራን ግን የኒውኪሌር ስምምነቱ እንዲጸና ፍላጎት አላት፡፡ በዋሽንግተን ማዕቀብ የኢኮኖሚ መገለል እንዳይደረግባት ዋስትናም ስፈልገገኛል ስትል  ኢራን መግለፃን የሮይተርስ ዘገባ አመላክቷል፡፡