የታሊባን ታጣቂ ቡድን መሪ ጃላላዲን ሀካኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የታሊባን ታጣቂ ቡድን መሪ ጃላላዲን ሀካኒ ከረጅም ጊዜ ህመም በኋላ መሞቱ ተነገረ፡፡

ሃካኒ ለረጅም አመታት በአፍጋኒስታን መንግስትና በአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል፡፡ 

በአፍጋኒስታን መንግስት ወታደሮችና በአሜሪካ ፀረ-ሽብር ኃይሎች ላይ ተደጋጋሚ ሽምቅ ውጊያ የሚፈፅመውና በቦንብ ፍንዳታ ካቡል ወደ ፍርስራሽነት እንድትቀየር ትዕዛዝ በመሥጠት ብሎም የሀክታኒ ኔትወርክ ቡድን በመምራት የሚታወቀው ጃላለዲን ሃክታኒ መሞቱ ታውቋል ።

ሃክታኒ ለረጅም ጊዜ በህመም ከተሰቃየ በኋላ መሞቱን ያስታወቀው ደግሞ የአፍጋኒስታን የሰቆቃ  ምድር እንድትሆን የሠራው አክራሪው የታሊባን ቡድን ነው፡፡

ቡድኑ አያይዞም ሀካኒ ረጅም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ መቆየቱን አሰታውሷል፣ ከዚህ ቀደም ግለሰቡ በአፍጋኒስታን መንግስትና አሜሪካ ጥምር ጦር በተደረገ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መሞቱ ሲነገር ቢቆይም ረጅሙን ጊዜ በህመም ማሳላፉ ታውቋል ።

አሁን ላይ በአካል ቢለየንም እሳቤዎቹና የጦርን ስልቱ ምዕራባውያንን ለመታገል የሚረዳን ስንቅ ነው ሲልም ታሊባን አስታውቋል፡፡       

የሀካኒ ኔትወርክ እኤአ በ1970 እንደመሠረተና ለበርካታ አመታት በበላይነት ሲመራው መቆየቱን ያስታወሰው ዘገባው መሪነቱን ለወንድ ልጁ ሰርዲን ሀኪን አስተላለፎ ነበር ፣ በአሁኑ ሰዓትም ልጁ የታሊባን ሁለተኛው መሪ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ።  

ሀኪን አሜሪካ የሩሲያን ጦር ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት በሚል ምክንያት ካቡል መግባቷን ተከትሎ ከታሊባን ታጣቂ ቡድን ጋር በመሆን ሽምቅ ጥቃት በመፈፀም ታዋቂነትን እያገኘ መምጣቱ ይነገርለታል ።

ከ2001 ወዲህ ከበርካታ ጥቃቶች ጀርባ መኖሩም ነው የሚነገርለት ፣ በመሠረተው ሀኪን ኔትውርክ አማካይነትም ጠላት ብሎ በፈረጃቸው የመንግስትና የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት እንዲፈፀም አመራር መሥጠቱ የሚታወቅ ሲሆን ታዋቂ ግለሰቦችን በማገትና በንፁሀን ላይ ሞትና ጉዳት በማድረስ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡

  በሀኪን የሚመራው ቡድን ጥቃት እንዲፈፅም ድጋፍ በማድረግ በኩል አፍጋኒስታንና አሜሪካ ፓኪስታንን ይከሳሉ ።(ምንጭ: የአልጀዚራ )፡፡