የደቡብ ኮሪያው መሪ ሙን ጄኤን ነገ ከሰሜን ኮርያ አቻቸው ጋር ይገናኛሉ

የደቡብ ኮሪያው መሪ ሙን ጄኢን ነገ ከሰሜን ኮሪያ አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን ጋር ፊት ለፊት እንደሚገናኙ  ተገለጸ ።

የሀገራቱ መሪዎች በሰሜን ኮሪያዋ መዲና ፕዮንግያንግ ሲገናኙ ሰሜን ኮሪያ የጸረ-ኒኩለር መርሃ ግብርን ተግባራዊ ከማድረግ እና በኢኮኖሚ ማዕቀብ ከመታመስ አንዱን እንድትመርጥ ይወሰናልም ነው የተባለው፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የደቡቡ አቻቸው ሙን ጄኢን በፕዮንግያንግ ሲገናኙ ሁለቱ መሪዎች በደንበራቸው አቅራቢያ በምትገኘው የወታደር አልባዋ ፓንሙንጆም ውጥረትን ማርገብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

ከሲዑሉ ሰማያዊው ቤተምግስት ለሮይተርስ የተሰጡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የመጀመሪያውን የወኪል ቢሮ በድንበራቸው አካባቢ ገንብተው አጠናቀዋልም፡፡

አሁን ላይ ግን በሁሌቱም ሀገራት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የምትታወቀው አሜሪካ ሁለቱ መሪዎች ሲገናኙ ዋነኛ አጀንዳ አድርገው እንዲመክሩበት የምትሻው የሰ/ኮሪያ የጸረኒኩለር መርሃግብር በምተገበርበት ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ከወራት በፊት አሜሪካ እና ሰ.ኮሪያ በሲንጋፖር ያስቀመጡት የሰ/ኮሪያ የጸረኒኩለር መርሃ ግብር ምንያህል ቁርጠኝነትን ያዘለ ነው የምለው ግን አሁን እንዳጠያየቀ ቀጥሏል፡፡

እናም ዋሽንግተን መሪዎቹ ዋነኛ ውጥናቸውን በዚህ ላይ እንዲያደርጉ ትሻለች፡፡ 200 ያህል የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን አካቶ በፕሬዝዳንት ሙንጄኢን ተመርቶ ወደ ሰ/ኮሪያ የምጓዘው የደቡብ ኮሪያ ሊኡክ በፕዮንግያንግ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ፊትለፊት የምገናኙ ይሆናል፡፡

ለዓመታት ተወጋግዞ እና ተራርቆ ለቆዩ ሀገራት ልዩ ክስተት የሆነው ይህ ክስተት ሁሌቱን መሪዎች በፕዮንግያንግ ሲያገናኘም የመጀመሪያው ነውና ለመላው ዓለምም በቀጥታ ስርጭት እንደሚደርስ ተጠብቋል፡፡

ማክሰኞ የምጀምረው የፕሬዝዳንት ሙን ጄኢን ከኪም ጆንግ ኡን ጋር የመገናኘቱ ጉዳይ የኮሪያ ልሳነ ምድር በ2 ከተከፈለ ወዲህ በአይነቱ ለ3ኛ ጊዜ ቢሆንም ከዚኛው ግንኙነታቸው በሁለቱ ሀገራት ጉዳይ ከመምከርም አልፎ የዋሽንግተን እና ፕዮንግያንግ የኒኩለር ጉዳይ ላይ በጥልቀት ተወያይተው መደምደሚያ ላይ እንደሚደርሱ ይጠበቃል፡፡

ዋሽንግተን አሁን ላይ የሰሜን ኮሪያ የጸረኒኩለር ፕሮግራም የምገታበትን እርግጠኛ ቀን ማወቅን ትፈልጋለች፡፡ በሌላ በኩል ፕዮንግያንግ የ1950ዎቹ የኮሪያ ልሳነምድር ጦርነት ማብቂያ የሚበሰርበት ጸጥታዋም የምረጋገጥበት የአሜሪካን ወታደሮች ከደቡብ ኮሪያ ምድር ማስወጣት እና ለዓለማቀፉ ማዕቀብ መነሳት ማስተማመኛን ትሻለች፡፡

ከአንድ ወር በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፐዮ ወደ ሰሜን ኮሪያ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞ በ11ኛ ሰዓት መሰረዛቸው የሚታወስ ነው፡፡

 ለዚህ ደግሞ የጠቀሱት ምክኒያት ከታሪካዊው የሲንጋፖሩ የኪም ግንኙነት ወዲህ ሰ/ኮሪያ የምታይ ምንም እርምጃ አላስመዘገበችም የሚል ነበር፡፡

አሁን ላይ ደግሞ የደቡብ ኮሪያው ፕሩዝዳንት ሙን ጄኢን የማሸማገል ሚናቸውን እንዲወጡ ሁሌቱም ሀገራት አሜሪካ እና ሰ/ኮሪያ ይፈልጋሉ ነው የተባለው፡፡

የሰሜን ኮሪያውን ጉዳይ በቅርበት የምከታተለው መቀመጫውን በሲዑል ያደረገው ፕሮፌሰር ላንኮቭ , ለአልጀዚራ  እንደተናገሩት የደቡብ ኮሪያ ልዑክ ፕዮንግያንግ ሲደርስ የትያትር ሚና ለመጫወት ካልሆነ በስተቀር እውነተኛ የሰሜን ኮሪያ የጸረ ኒኩለር ትግበራ ላይ መድረስ የሚቻል አይደለም ይላሉ፡፡

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪ ሙን ጁን ኢ , ደግም የሰሜን ኮሪያ የ ጸረ ኒኩለር ዘመቻ ግቡን የምመታው በህዴት ብቻ መሆኑን ያምናሉ፡፡ በአሁኑ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በፕዮንግያንግ ሲገናኙም ሰ/ኮሪያ የኒኩለር ፕሮግራሟን በምትገታበት እና አሜሪካም የማእቀብ ጋጋታዋን በምታነሳበት አግባብ ላይ እንዲወያዩ ብቻ የሚጠበቅ መሆኑን ነው አማካሪው ለመገናኛ ብዙሃኑ ይፋ ያደረጉት፡፡