የብሪታንያው ሌበር ፓርቲ ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት የጀመረችውን ሂደት ማቆም እንዳለባት አስታወቁ

የብሪታንያው ተቃዋሚ ፓርቲ ሊበር ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት አባልንት ለመውጣት እያደረገች ያለውን ሂደት ማቆም እንዳለባት አስታውቋል፡፡

ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት ካቀረበችበት እና ምርጫ ከተካሄደ 2016 ጀምሮ የተለያዩ ሓሳቦች ሲሰተናገዱ ቆይተዋል፡፡

በቅርብ ጊዜ እንኳን የሀገሪቱ ነጋዴዎች ሀገሪቱ ከአውሮፓ ህብረትነት ለመውጣት እያደረገችው ያለው ሂደት በንግዱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረባቸው እንደሆነ እና ከሌሎቹ የህብረቱ ሀገራት ጋር ያላቸው የንግድ ግንኙነት መቀዛቀዙን ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ከተለያየ አቅጣጫ የተለያ ሓሳቦች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ የብሪታንያው ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ሌበር ሀገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ እንድታቆም እና ፓርቲውም ይህንን ሙሉ በመሉ እንደማይቀበል በጋራ ስምምነት ማፅደቁን አስታውቋል፡፡

ፓርቲው በሠጠው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው ከሆነ ብሪታንያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ያደረገችውን ምርጫ ልትደግመው እንደሚገባ እና እነሱም ሀገሪቷ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት እንዳትወጣ እንሰራለን ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ጀርሚይ ኮርባይን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የተቃዋሚ ፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣናት  የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ሀገሪቱ ከህብረቱ አባልነት እንድትወጣ የሚያቀርቡትን ማንኛውንም ጥያቄ እንደማይቀበሉ በዚህ ጉዳይ ያላቸውን የፀና አቋምም ያስታወቁ ሲሆን ሀገራቸው የህብረቱ አባል ሆና እንድትቆይም የተቻላቸውንም እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ የቴሬዛ ሜይ ሓሳብ ተከታዮች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያነሷቸው ሓሳቦች ፈፁም የተራራቁ ከመሆናቸውም ባለፈ ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ብሪታንያ ከህብረቱ አባነት እወጣለሁ ብላ ባቀደችው ጊዜ ላትወጣ እንደምትችል እና ሊጎተትም ይችላል የሚል ሓሳብ ያነሳሉ፡፡

ከዛም ባፈ ብሪታንያ አሁን እያሰተናገደቸው ባለው ሁኔታ ከቀጠለች በ2016 ያደረገችውን ምርጫ ዳግም ልታካሂድ እንደምትችላተንታኞቹ ይገልፃሉ፡፡(ምንጭ:ቢቢሲ)