በብራዚል ምርጫ የግራ ዘመም መሪው ፌርናንዶ ሃዳድ የቀኝ ዘመሙን ጃይር ቦልሳኖር ለማሸነፍ ተዓምር ያስፈልጋቸዋል ተባለ

በብራዚል ብሔራዊ ምርጫ የግራዘመም ፖለቲካ አቀንቃኙ ፌርናንዶ ሃዳድ ቀኝ ዘመሙን ሰው ጄይር ቦልሶናሮ ለማሸነፍ ተዓምር ያስፈልጋቸዋል እየተባለ ነው፡፡

በዚህ ቀጣይ ሶስት ሳምንታት እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የብራዚል ምርጫ 13 እጩ ተወዳዳሪዎች ሲፎካከሩ የነበረ ሲሆን አሁን በ2ኛ ዙር የተወዳዳሪነት ፉክክሩ በሁለቱ ሰዎች መሃል ሆኗል፡፡

በአውሮፓውያኑ ቀን ቀመር ጥቅምት 28 ቀን 2018 በሚካሄደው የብራዚል ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የፌርናንዶ ሃዳድ እና የጀይር ቦሶናሮን ፉክክር ተንታኞቹ ከከባድ ሚዛን የቦክስ ውድድር ጋር እያመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡

በተለይም ደግሞ ከወዲሁ ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገለት እንደሚገኝ የሚነገርለትን የቀኝ ዘመም ፖለቲካ ርዕዮት አቀንቃኙ ጀይር ቦልሶናሮን ለማሸነፍ ፌርናንዶ ሃዳድ መሃል ሰፋሪዎቹን ወደ እራሳቸው በመውሰድ ከባድ የቤት ሥራ እንዳለበት ነው ተንታኞቹ የሚገልጹት፡፡

ብራዚል ባሳለፍነው እሁድ ባደረገችው ብሄራዊ ምርጫ የሶሻል ሊብራል ፓርቲው ሰው ጀይር ቦልሰናሮ, 46 ከመቶ ድምጽ በማግኘታቸው በጠባብ ውጤት ምርጫውን ሳያሸንፉት ቀርተዋል፡፡

የሠራተኞች ፓርቲው ፌርናንዶ ሃዳድ, ደግሞ ዘብጥያ የወረዱትን የቀድሞ የብራዚል መሪው ልዊዝ እንያስዮን "ሉላ" ዳሲልቫን  ተክተው በመወዳደር ነው 29 ከመቶ የሚሆን ድምጽ በማግኘት ለመጨረሻ ዙር እጩ ተወዳዳሪነት የደረሱት፡፡

እናም አሁን ከዚህ በኋላ ሀዳድ የማሸናፋቸው ነገር ታምር ካለተከሰተ ቦልሶናሮን መርታት እጅግ ከባድ እንደሚሆንባቸው እየተነገረ ይገኛል፡፡  በራስ መተማመንና ከሉላ ተፅዕኖ ስር በመውጣት የሚያሳዩት አቋም ምናልባትም ነገሮችን ሊለውጥ ከቻለ የሚል መላምት እየተነሳ ይገኛል ።

ባለፈው እሁድ የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ ከ21 ቀናት በኋላ ውጤቱን ለመቀልበስና የበላይነቱን ለመቀዳጀት ድምፃቸውን ለቦልሰናሮ የሠጡ መራጮችን ልብ መሸፈት ይጠበቅባቸዋል፡፤ ከፍ ሲል ደግሞ በወንጀልና በፀጥታው ረገድ ያላቸውን ፖሊሲ መፈተሸ ለሀዳድ ቀጣይ የቤት ሥራቸው ሆኖ ተቀምጧል ።

አናም ሀዳድ አብላጫውን ድምፅ ለማግኘት ከምን ጊዜውም ከባድ ጊዜ ውስጥ ናቸው፡፡ በመጀመሪያው ምርጫ  የሲሮ ጎሜዝንና ድምፅ ያልሠጡ ዜጎችን ልብ ማሸነፍ ከቻሉ ብቻ ምናልባት ሊረቱ እንደሚችሉ  ቲያጎ አርጋጎ የተባሉ በብራዚል መቀመጫውን ያደረገው አርኮ የፖለቲካ አማካሪ ድርጅት ምሁር ተናግረዋል፡፡

የቦልሶናሮን ተቀባይነት ለመቀልበስ የሚያስችል ስልትና ያላቸውን መልካም ዝና መገዳደር የሚችሉበት አካሄድም ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ አስረድተዋል ።

ሲሮ ጎሜዝ በአሁዱ ምርጫ 12ነጥብ5 በመቶ ድምፅ ያገኙ ሲሆን 30 ሚሊዮን የሚጠጉት ደግሞ ድምፅ ከመስጠት የተቆጠቡ ናቸው፡፡

ሀዳድ ይይንን እድል በስልታዊ አካሄድ የራሳቸው ማድረግ ከቻሉና በተጨማሪም የምርጫው እለት በሚጠበቀው ክስትት ጭላጭል የማሸነፍ ተስፍ እንዳላቸው የሚያነሱ ጥቂቶች ተሰምተዋል ፣  ምንም እንኳን በርካቶች አሸናፊነቱን ለቦልሶናሮ ቢያደርጉትም ።

ቦልሶናሮ በቅስቀሳና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የማይተሙና የመራጮችን ልብ በፖሊሲ አማራጭ በመግዛት መጪው ምርጫም ለውጥ እንደማይኖረው ደጋፊዎቻቸው እየተነገሩ ነው፡፤ ለዚህም ሲባል የሀዳድ የማሸነፍ እድል በርሳቸው አካሄድ እንደሚወሰን በመነገር ላይ ነው፡፤

በአሁኑ ሰዓት በብራዚል 13 ሚሊዮን ህዝብ ስራ ፈላጊ በሆነበትና በወጥ የፖለቲካ እይታ እየተመራ እንዳልሆነ በሚነገርለት ምርጫ የሀዳድ ቦልሶናሮን የማሸነፍ ጉዳይ አነጋገሪ ሆኖ ቀጥሏል፡፡( ምንጭ: አልጀዚራ )